Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Clergies & Parishioners Association 

The association will organize, mobilize and make plans to defend and protect the holy EOTC at any level. 

Mission of the project



How do we accomplish our Mission 

Define the Goal

Clearly define the goals and objectives of the project. What problem are you trying to solve, and what outcomes do you hope to achieve? Be specific about what you want to accomplish.


Identify Stakeholders

Identify all the stakeholders who will be involved in the project. This includes team members, partners, vendors, and any other individuals or organizations who have an interest in the project's success.

Assign Responsibilities

Assign specific responsibilities to team members and stakeholders to ensure everyone knows what they are responsible for and what is expected of them.

Establish Communication Channels

Establish communication channels to keep all stakeholders informed of project progress and any changes that may impact the project's success. This could include regular team meetings, progress reports, or status updates.

በመጪው ረቡዕ ጥቅምት ፭ ቀን ፳፻፲፯ ዓም የተጠራ ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ

October 12, 2024 4:17:23 pm. 

በመጬው ረቡዕ የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው የካህናት እና የምእመናን ኅብረት፤ በአካባቢያችን ካሉት የተለያዩ የማኅበረሰብ እና ሲቪክ ማኅበራት ጋር በመተባበር ታላቅ የሰላምዊ ሰልፍ ተዘጋጅቷል፤ በሀገራችን ኢትዮጵያ በፋሽቱ መንግሥት የሚፈሰው የንጹሐን ደም፣ የድሮን ድብደባውን፣ የካሕናት መታረድ፣ የንጹሐን ዜጎች በተለያዩ ቦታዎች በእሥር መንገላታት፣ የዜጎችን በልማት ሰበብ ጎዳና ተዳዳሪ ማድረግ የመሳሰሉትን በመንግሥታዊ የሆንውን ጥፋት እና ግድያ ለአለም ሰላም ወዳድ ማኅበረሰብ ለማሳወቅ እና ተቃውሟችንን ለመግለጽ በOctober 16, 2024 at State Department 2201 C Street, NW. Washington, DC የተቃውሞ ሰልፍ ተዘጋጅቷል፤
ኢትዮጵያውያን በሙሉ ድምጽ ለሌለው ወገናችን ድምጽ እንሁን በማለት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፤ ማንም ሰው በተቻለው መጠን ይሄንን ግፍ እና እንግልት የሚቃወም በሙሉ በዚህ ሰልፍ ላይ ታዳሚ እንዲሆን በአክብሮት እንጋብዛለን።
በዚህ ቀን በተለያዩ ከተሞች በተመሳሳይ ጊዜ ተቃውሞው የደረጋል፤ ከነዚህም መካከል
በለንደን                                      በጀርመን
በካናዳ

አዘጃጆች ፡
* የዋሺንግተን የካህናት እና ምእመናን ኅብረት
* የዋሺንግተን ዲሲ የጋራ ግብረኃይል
* EAPAC (American Ethiopian Public Affairs Committee)
* WAAA (Washington Area Amhara Association) 
* ዓለም አቀፍ የአማራ ኅብረት
* አማራ ትንሣኤ                                

ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ጳጉሜ ፪ ቀን ፳፻፲፮ ዓም

September 6, 2024 11:21:36 pm 

ነገ ጳጉሜ ፪ ቀን ፳፻፲፮ ዓም ከ2፡00 ፒኤም ጀምሮ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ በደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ዋሺንግተን ዲሲ ይደረጋል፤ ብንችል በአካል፤ ካልቻልን ግን በዙም በመገኘት የጉባኤው ተሳታፊ እንዲሆኑ በአክብሮት ተጠርተዋል፤ 

ብፁዕ አባታችን አቡነ ሉቃስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአውስትራሊያ እና ኒውዝላንድ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቦታው በመገኘት ቡራኬ እና ቃለ ምዕዳን ይሰጣሉ፤ በርከት እና ጠንከር ያሉ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ችግሮች ከነ መፍትሄዎቻቸው ይቀርባሉ፤ ለቅድስት ቤተክርስቲያን መፍትሄ መፈለግ የሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን መብትም ግዴታም ነው፤ ስለዚህ በቦታ ተገኝተው የመፍትሄው አካል ይሁኑ። 

Meeting ID: 833 4475 6991
Passcode: EOTC 

2:00 pm - 6:00 pm 

አብዛኛውን ጊዜ የውይይት፣ የጥያቄ እና መልስ በመሆኑ በቦታው በመገኘት የመፍትሄው አካል ይሁኑ፤ 

የካህናት እና ምዕመናን ኅበረት በዋሺንግተን ዲሲ 

ታላቅ መንፈሣዊ ጉባኤ ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ 

July 15, 2024 9:15 PM 

በመጪው ወር ማለትም ጳጉሜ ፪ ቀን ፳፻፲፮ ዓም (September 7, 2024) ታላቅ መንፈሣዊ ጉባኤ ይደረጋል፤ በጉባኤም ላይ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ዘማሪያን፣ ሰባኪ ወንጌላውያን፣ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ ምዕመናን እና ምዕመናት፤ ይገኛሉ፤ 

ስለወቅቱ የቤተክርስቲያን ፈተናዎች እና መፍትሔዎቻቸው በተጋባዥ የጥናት ጽሑፍ አቅራቢዎች ዳሰሳ ይደረጋል፤ አብዛኛውን ጊዜ ምዕመናን እና ምዕመናት በሚሰጡት የመፍትሔ ሃሳቦች እና የሚሰጡትን አቅጣጫዎች ያገናዘበ ሰፊ የውይይት ጊዜ ይኖረናል፤ እዳያመልጥዎት፤ እንላለን። 

አምላከ ቅዱሳን ለሃገራችን ሰላምን፣ ለቤተክርስቲያንም ትንሣኤዋን ያቅርብልን አሜን።
የካህናት እና ምዕመናን ኅብረት በዋሺንግተን ዲሲ 

ብፁዕ አቡነ ሉቃስን ጉብኝት

June 20, 2024 10:14 PM

የካንህናት እና ምዕመናን ኅበረት ዋሺንግተን ዲሲ በብፁዕ አቡነ ሉቃስ መኖሪያ ቤት በመገኘት ከብፁዕነታቸው ቡራኬ እና ምክር ተቀብሎ ተመልሷል።
ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የአውስትራሊያ እና የኒውዝላንድ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሰሜን አሜሪካ ከመጡ ከሁለት ወራት በላይ አስቆጥረዋል፤ ማኅበሩም የብፁዕነታቸውን ቡራኬ ለመቀበል እና ለመጎብኘት ብሎም ከብፁዕነታቸው ጋር መክፈልት በጋር ለመቋደስ ተገኝቶ የብፁዕነታቸውን ቡራኬ እና ምክር ተቀብሏል።
ብፁዕነታቸውም በምክራቸው በርቱ፤ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ ፈተና እና ሕመም ላይ ናት እንደ እናንተ አይነት ልጇቿን ደግሞ አምላከ ቅዱሳን አያሳጣት ፤ በርቱ የምትችሉትን አድርጉ በዚህ ዘመን እጅግ ፈተና በበዛበት ከእናት ቤተክርስቲያን ጎን መሆን ከሁሉም በላይ ትልቅ በረክት የሚያስገኝ ስለሆነ በክፉም፣ በደጉም ፤ በማጣትም፣ በማግኘትም ጊዜ ቤተክርስቲያንን እንዳተዉ በማለት ምክራቸውን ለአባላቱ ሰጥተዋል።
የብፁዕነታቸው ቡራኬ ይደርብን አሜን። 

የአቋም መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ 2024.pdf

የካህናትና ምዕመናን ኅብረት ሰሜን አሜሪካ ያወጣው መግለጫ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በያሉበት፤

   ግንቦት ፲፰ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም.
EOTC CPANA09182106

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ወይእዜኒ ዕቀቡ ርእሰክሙ ወኲሎ መራዕየ ዘሎቱ ሤመክሙ መንፈስ ቅዱስ ጳጳሳተ ከም ትርዐዩ ቤተ ክርስቲያኑ ለክርስቶስ እንተ አጥረያ በድሙ

በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። የሐዋርያት ሥራ ፳፰

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የካህናት እና ምዕመናን ኅብረት በሀገራችን ኢትዮጵያና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተለያዩ ፈተናዎች ሲከሰቱ በኛ በኩል ልናደርግ ይገባል ብለን ያመንበትን ኃሳብ ስናቀርብ ቆይተናል። ችግሩም ከዕለት ወደ ዕለት እየሰፋ መምጣቱን ተከትሎ ያለብንን መንፈሳዊና ሃይማኖታዊ ግዴታ ለመወጣት እንድንችል በጥምረት ሆነን የተቻለንን ሁሉ በማድረግ ላይ እንገኛለን።

ከሀገር ርቀን የምንገኝ ካህናትና ምዕመናን ብንሆንም በየወቅቱ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደርሰው መከራና ሰቆቃ በእኛ ላይ እንደ ደረሰ ያለ መሆኑን እያሰብን ለቤተ ክርስቲያንና ለወገኖቻችን በውጭው ዓለም ድምጽ ለመሆን እየሰራን እንገኛለን።

ከዚህ በፊት ከተደረጉ ተግባራት መካከል በጥቂቱ ለመግለጽ፦

1/ ለአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በሀገራችን እና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየተደረገ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በሰላማዊ ሰልፍ ወጥተን ግንዛቤ አስጨብጠናል።

2/ ጥር 14 ቀን 2014 . የተደረገው የጫካ ሲኖዶስ ሕገ ወጥ ሲመት በሀገራችን እና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት በአሜሪካ ዋና ከተማ እንደመኖራችን በዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥት አደባባይ ቀርበን የተጋረጠውን አደጋ በማስረዳት ኃላፊነት የሚሰማቸው አካላት ሁሉ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ በተደጋጋሚ አሳስበናል።

3/ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአፍሪካ ጉዳዮች ኮሚቴ የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገራችን በሕዝባችን እና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሃይማኖት ጣልቃ ገብነት፤ በሲኖዶሱ ውስጥ እያደረገ ያለውን መከፋፋል  እንዲያቆም በሰላማዊ ሰልፍ እና በደብዳቤ ጠይቀን የጽሑፍ መልስ አግተናል።

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት

ከላይ በመግቢያ የዘረዘርነው ነጥብ ከታሪክ ተወቃሽነት ራሳችሁን እና ቤተ ክርስቲያናችሁን እንድትታደጉ የበኩላችሁ ጥረት እንድታደርጉ ለመማጸን ነው እንጂ እየሆነ ያለው ነገር ከናንተ የተሰወረ እንዳልሆነ እንረዳለን፡፡

በአሁኑ ሰዓት በውስጥም በውጭም በተደራጁ አካላት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የታቀደውን የማፈራረስ ሴራ አላወቅንም ያሳሰበን የለም ችግሩን የፈጠሩት  እነ እገሌ ናቸው ብሎ የሚታለፍ እንዳልሆነና በዘመናችሁ አሳዛኝ እና አስከፊ የታሪክ ጠባሳ ጥላችሁ እንዳታልፉ፤ ደማቸው በከንቱ በግፍ እየፈሰሰ ያለውን የወገኖቻችን መከራ ለአፍታ በዐይነ ሕሊናችሁ ትዝ እንዲላችሁ፤ እኛም ከሕሊና ወቀሳ ነጻ እንድንሆን አስቀድመን የተሰማንን ኃሳብ መግለጽ አስፈላጊ ስለሆነ ነው።

በዚህ መነሻነት በዘንድሮው 2016 .  ርክበ ካህናት  የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት  በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ እየመጣ ያለውን  እጅግ ከባድ እና አስፈሪ ፈተና በጥብዓት ማለፍ ትችሉ ዘንድ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ኃሳባችንን እንዲጋሩን የሚከተለውን የአቁም መግለጫ አውጥተናል፡፡

የአቁም መግለጫ

1/ መጪው ዘመን እና ጊዜ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እጅግ ፈታኝ አስፈሪ በመሆኑ በርካቶች የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባላት መንግሥትና ቅጥረኞቹ ባቀዱትና በሸረቡት ሀገርንና ቤተ ክርስቲያንን የማፈራረስ በጎጥ የመከፋፈል ዕቅድ አስፈጻሚ እንዳትሆኑ መጭውን ጊዜ አባቶቻችን በጸሎት እና በጽሞና እንድታሳልፉ በአክብሮት እንጠይቃለን፤

አንዳንድ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለሥልጣንና ለጥቅም አሳልፎ በመስጠት ታሪካዊ ስህተት በመሥራት እና ኃላፊነታቸውን ባለመወጣት ከእግዚአብሔር ለተቀበሉት አደራ በምንደኛነት ተሰልፈው እናያቸዋለን፣ አብዛኛው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ግን ከዚህ አሉታዊ ተግባር እንድትቆጠቡ በልጅነት ጥያቄያችንን እናቀርባለን። ከሐዋርያት የተቀበልናትን ቅድስት ቤተክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ ከእግረ መስቀላችሁ ሥራ ወድቀን እንጠይቃለን።

2ኛ/ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በግፍ ወደ ሃገራቸው እንዳይገቡ ሲደረገ፣ በዚህ ሰሞን ደግሞ ሌሎች ብፁዓን አባቶች በቅርቡ ወደ ሃገር ለርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ለመሳተፍ ሲመጡ እንዳይገቡ ሲከለከሉ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ አሁንም በዝምታው ጸንቷል፤ በመሆኑም ይህ ድርጊት በአስቸኳይ ካልቆመ ቤተ ክርስቲያኒቱን የማዳከም እንቅስቃሴ ስለሚጨምር በአስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊውም ሆነ ሌሎች አባቶች ወደ ሃገራቸው መግባት እንዲችሉ የሚመለከተው አካል ግፊት እንዲያደርግ እንጠይቃለን።

3ኛ/ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ቅዱስ ፓትርያርኩ እና  ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በቢሯቸው ጠርተው ሲያነጋግሩ ካነሱት ነጥብቤተክርስቲያን የነፍሰ ገዳይ ማሰልጠኛ ሆናለችከእናንተ ውስጥ ገንዘብ የማይቀበል አለ ብዬ አላምንምየሚሉና ሌሎችም የቤተ ክርስቲያናችንን ክብር የሚያጎድፉ   ሃይማኖቷን የሚያሳንሱ እጅግ ጸያፍ ክብረ ነክ የሆነ ነገር በስብሰባ ላይ ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ በዕለቱ ምንም መልስ ወይም ማብራሪያ እንደማይቀበሉ ይታወቃል፤ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ሚዲያ ወይንም በሌሎች ሚዲያዎች በመጠቀም፤

·         ቤተ ክርስቲያን የድኅነት ቦታ እንጂ የወታደር ማሰልጠኛ አለመሆኗን በጠቅላዩ የተባለው ፍጹም ስህተት መሆኑን፤

·         የቅዱስ ሲኖዶስም አባላት በገንዘብ የሚገዙ ወንጀለኞች ናችሁ ብሎ ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ የተነገረው እጅግ ስህተት መሆኑን፤

·         በአገዛዙ የተመለመሉ፤ በካድሬነት የተሰማሩ የክህነት መልክ ያላቸው ተወካዮች ነን ባዮች፤ መንግሥትን ለምን የራስህን ፓትርያርክ አትመርጥም በማለት የተናገሩትን ቤተ ክርስቲያኗን አሳልፈው የሰጡትን አባት ተብዬዎች ለአማኙ ሕዝብ በማሳወቅ ቀጣዩን ፈተና በጥንቃቄ ለመወጣት ጥረት እንዲደረግ እንጠይቃል።

4ኛ/ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሉቃስ እውነትን ስለተናገሩ በመንግሥት ሲከሰሱ ሌሎች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከብፁዕነታቸው ጎን መቆም ሲገባቸው በአብዛኛው ዝምታን መርጠዋል፤ ጥቂት አባቶች ደግሞ ግፍ ከሚፈጽመው አካል ጎን ቆመው ብፁዕነታቸውን መዝለፋቸው ሳያንስ በመጪው ርክበ ካህናት ላይ ብፁዕነታቸውን ለማስወገዝ ከጌቶቻቸው በተቀበሉት ተልዕኮ ጠዋት እና ማታ ሲሮጦ በማየታችን እጅግ አዝነናል፤ ቅዱስ ሲኖዶስ በብፁዕነታቸው ላይ ምንም አይነት እርምጃ ከወሰደ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ትልቅ ክፍፍል ስለሚፈጥር ጉዳዩን በጥንቃቄ እንዲይዘው እያሳሰብን በብፁዕነታቸው ላይ የተከፈተውን የወንጀል ክስ እንዲያስቆም እና ከብፁዕነታቸው ጎን እንዲቆም እንጠይቃለን።

5በተለያዩ የሀገራችን ክፍል በተለይ በአርሲ አካባቢ በመንግሥት አካላት የሚገደሉት፣ የሚታረዱት ብሎም የሚቃጠሉትን አብያተ ቤተ ክርሲቲያናት በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ምንም አይነት የተቃውሞ ወይም ጥያቄ አለማቅረብ ማኅበረ ካህናትን እና ምዕመናንን በእጅጉ ያሳዘነ ተግባር ነው፤ ቅዱስ ሲኖዶስ በአስቸኳይ ጉዳዮችን አጣሪ ክፍል በማዘጋጀት  አስቸኳይ ምላሽ እና መግለጫ ወይም የሚመለከተውን አካል ትብብር የመጠየቅ ወይም የመከለካለ ሥራ እንዲሰራ የሚያደርግ አሰራር መቀየስ ወይም እንዲያስተባብር  እንጠይቃለን፡፡

6/ በጥር ፲፬ ቀን ፳፻፲ .. በጫካ የተደረገውን ሕገወጥ ሲመት ተከትሎ በሻሸመኔ በርካቶች ክቡር ሕይወታቸውን ሰውተዋል፣ ያንን ተከትሎ ጥቁር በመልበስ ዘመቻው ከሥራቸው የተፈናቀሉ፣ እስከ አሁን በእስር ላይ የሚገኙ ክርስቲያኖች በምን ሁኔታ እንዳሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ሥራ አስኪያጅ ወይም ጸሐፊ ወይም በየደረጃው ያሉ የሥራ ኃላፊዎች ክትትል በማድረግ የማጽናናት፣ ወይም ለማስፈታት የተደረገ  ሙከራ ካለ መልካም ከሌለ ግን እኛንም በእጅጉ እያሳዘነን ስለሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጀንዳ ተወያይቶ ለሚመለከተው አካል ጥያቄ በማቅረብ የሚደርስበትን ውጤት በይፋ እንዲገልጽልን በአክብሮት እንጠይቃለን።

7/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንጀራዋን በልተው መውጫ መግቢያውን በሚያውቁ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶቿ በቅንጅት ለማፍረስ የሚደረገውን ርብርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ሕገ እግዚአብሔርን፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን መሠረት አድርጎ ከምንም በላይ አንድነቱን፣ ማዕከላዊ የመዋቅር አደረጃጀቱን እና ሉዓላዊነቱን አስጠብቆ  በዚህ  የግንቦት 2016 . ርክበ ካህናት ጉባኤ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አጥብቀን እንጠይቃለን።      

8/ ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያው ተሰራጭቶ የታየውና ጉዳይም ከሚመለከታቸው ጋር በተደረገው ማጣራት ሁለት ሊቃነ ጳጳሳት ማለትም  ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስና አቡነ ያዕቆብ ወደ ሀገር ቤት እንዳይገቡ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉዙ ትኬታቸውን መሠረዙ ታውቋል። ይህ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን አንድነቷን ለማሳጣት መንግሥት የሚያደርገው የመከፋፈል ሤራ በመሆኑ እየተቃወምን ቅዱስ ሲኖዶስ አጠቃላይ መፍትሄ እንዲያስቀምጥ እንጠይቃለን፤

9በመላው ዓለም ላይ ያለን ካህናት እና ምዕመናን ሁላችንም በቤተ ክርስቲያናችንና በገዳማቱ ፣ በአብነት ትምህርት ቤቶቻችንና ታሪካው የቅድስና ሥፍራዎችን በማጥፋት ሕዝበ ክርስቲያኑን በመጨፍጨፍ ሊቃውንቱን በመግደል በተጠና ዕቅድ የብልጽግና መንግሥት የሚፈጽመውን የዘር ማጥፋት እንቃወማለን፡

10ኛ/ የዲሲ እና አካባቢው የካህናትና ምዕመናን ኅብረት የሰው ዘር ለተባለው ሁሉ ይልቁንም መከራው ለጸናበት ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያንን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት አገራችንን ኢትዮጵያንም ለማፍራረስ የሚደረገውን ርብርብ እየተቃወምን ወገኖቻችንን  በምንችለው ሁሉ  ድጋፍ ለማድረግ እና ለማስተባበር ቅዱስ ሲኖዶሱም አንድነቱን ጠብቆ የመንደር ሲኖዶስን በማረቅ፤ በአቋሙ ጽንቶ ለሚያደርገው ጥረት ሁሉ ድጋፋችንን እናበረክታለን።      

 ማጠቃለያ

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤-

 በአጠቃላይ በሀገራችን ኢትዮጵያ የሃይማኖት ነጻነት ከምድሪቱ እየጠፋ እንዳለ እና ቅዱስ ሲኖዶስም ምንም አይነት ጥያቄ አለማቅረብ፤ በተለይ መንግሥት የሚያደርገውን የሃይማኖት ጣልቃ ገብነት በዝምታ ማለፍ ተገቢ ባለመሆኑ ከላይ 1-10  የጠቀስናቸውን ነጥቦች ከግንዛቤ ውስጥ በመክተት በቅንነትና በማስተዋል ልትረዱት ይገባል ብለን እናምናለን፡፡ በተቃራኒው ለጥቅም ተገዝተው ኃላፊነታቸውን ዘንግተው ለአገዛዙ ወኪል በመሆን ለሚያስጨንቋችሁ ቡድኖች ወይም ካድሬዎች ቤተ ክርስቲያኗን አሳልፋችሁ በመስጠት ቤተ ክርስቲያኗን በማፍረስ ተልዕኮ ውስጥ በመሳተፍ ለምትወሰኑት ውሳኔዎች ሁሉ ከታሪክ ተወቃሽነት እንድትድኑ እና በመልካም ሥራ ሰርተው እንዳለፉት ሐዋርያት አባቶቻችሁ አሰረ ፍኖታቸውን ትከተሉ ዘንድ አስቀድመን እያሳሰብን እኛም እንዲህ ያለውን አካሄድ በመደገፍ አንድነታችንን አጠናክረን ከእውነተኞቹ ጎን በመቆም ማንኛውም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናችንን በታላቅ ትህትና  እንገልጻለን።



                                 ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬያችሁ ይድረሰን!

                                      ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር

 

 

                          እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን በረደኤት ይጠብቅልን፤                   

ግንቦት 18 ቀን 2016 .

(May 26, 2024)   Washington DC

 

ግልባጭ

+ ለመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት

+ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ

+ ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በየአህጉረ ስብከታቸው

+ ለማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያና ኦዲዮ ቪዡዋል ክፍል

+ በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ ማኅበራት በሙሉ


የኅብረቱ የአቋም መግለጫ በማኅበራዊ ሚዲያ

EOTCCPA Meglecha.mp4

የኅብረቱ የአቋም መግለጫ በቪዲዮ

State Department Response.pdf

Ms. Molly Phee, Bureau of African Affairs responded to our letter.  

May 14, 2024, 3:13 pm

Last April 23, 2024, we had a public rally from Capitol Hill to the State Department, during our rally we presented a letter of concern to the Bureau of African Affairs head of special assistance Ms. Molly Phee. 

The special assistance secretary of state responded to our concern on May 9, 2024, and we appreciated the response we will continue to knock doors of all public officials plus other US government public officials as well. 

EOTCCPAkesisMulugeta.pdf

በመልአከ ሣህል ሙሉጌታ ወንድሙ ከማኅበሩ ሃላፊነት ስለመነሳት የተሰጠ መግለጫ

    መጋቢት ፳፰ ቀን ፳፻፲፮ ዓም                                                                                                         

EOTCCPA-RE2016728

 

ለመልዓከ ሣህል ሙሉጌታ ወንድሙ ባሉበት

 

ጉዳዩ፤ የካህናትና ምእመናን ኅብረት መረጃዎችን እና ማንኛውንም የሕብረቱን ንብረቶች ስለማስረከብ

በሰሜን አሜሪካ የካህናትና ምእመናን ኅብረት የተቋቋመው በሀገራችን ኢትዮጵያ በተዋህዶ ቤተ ክርቲያንና አማኞቿ ላይ ታቅዶና ተጠንቶ እየተፈጸመ ያለውን ሥር ነቀል ጥቃት ተከትሎ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጉዳዩን እንዲረዱት እግዚአብሔር በነጻው ዓለም ላይ እንድንኖር የፈቀደልን ካህናትና ምእመናን በጥምረት ተዋህደን በስማችን ሕጋዊ ፈቃድ ከሚመለከተው ክፍል እንዲወጣ በማድረግ የተለያዩ ስብሰባዎችን በማካሔድ የውስጥ መመሪያና የሥራ ድርሻ ቀርጸን ተገቢውን ሁሉ ስናደርግ እርስዎም የማኅበሩ ጸሐፊ ሆነው እንዲያገለግሉ በዚሁ ጉባኤ ተሰይመው ከዋና ሰብሳቢውና ከምክትል ሰብሳቤ ጋር በመሆን አባላቱን በማደራጀት፤ የስብሰባውን ሰዓት በማቀናበር የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ በማውጣት የተጣለብዎትን ኃላፊነት ሲወጡ መቆየትዎን የምነዘነጋ አይደለንም

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


EOTC CPA-Final released-030524.pdf

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

ካህናትና ምዕመናን ኅብረት የጋራ የአቋም መግለጫ

March 15, 2024 10:24 pm


በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የካህናትና ምዕመናን ኅብረት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተውሕዶ ቤተክርስቲያን እየደረሰ ባለው መጠነ ሰፊ ግፍ እና እንግልት ዙሪያ እንዲሁም በደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መን ፈሥ ቅዱስ ገዳማውያን ላይ የደረሰውን እጅግ ዘግናኝ እና አረመኒያዊ ተግባር በማውገዝ እና መንግሥትም ደሃ እንዳይበደል ፍርድ እንዳይጓደል የማድረጉን ሥራውን መዘንጋቱን ለማስታወስ ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥቷል፤ መግለጫውን በዚህ እንደሚከተለው ሙሉውን ያገኙታል።

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 

Don't miss the conversation! 

June 22, 2023 11:24 pm

On the coming Wednesday June 28, 2023 at 8:00 pm, we will have very distinguished guests Dr. Yonas Birru and Memher Fantahun Wake, discussing the current situation in Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. 

Please join us on zoom from where ever you might be and be part of the discussion. 

Dial in number : 646 749 3112
Passcode : 565109429

Public Meeting with
Lique Mameran Fentahun Muchie

May 1, 2023 11:25 am 

Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Clergies & Parishioners Association will held a public meeting on Saturday May 6, 2023 at 2:00 pm at Saint Gabriel Cathedral of Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Washington DC. 

The event will cover all the government interference with our church and will discuss how we call prevent such intervention, the association will have ideas how we all involve with the solution. 

Let's all come and be part of the solutions. 

2601 Evarts Street. NE. Washington, DC 20018


አስቸኳይ የሰላም ጥሪ ለኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለመንግሥት እና ባለድርሻ አካላት በሙሉ!

Questions?

Contact eotcdcp.assn@gmail.com to get more information on the project

FacebookTwitterYouTube